የቡናና ሻይ  ባለስልጣን የሀገራችንን ዋነኛ የወ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

የቡናና ሻይ  ባለስልጣን የሀገራችንን ዋነኛ የወጭ ምርት እሴት በመጨመር  ኤክስፖርት ማድረጉ የሚበረታታ መሆኑን ምክትል ከንቲባ  እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር  አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር  አቶ ጃንጥራር አባይ ከUNIDO ተወካዮች ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ  ባለስልጣን የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በባለስልጣኑ ቢሮ እና የምርት ማሳያ ላይ ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝቱም ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር  አቶ ጃንጥራር አባይ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሀገር ዋልታ የሆነውን የቡና ምርት እሴት በመጨመር ተጨማሪ ዶላር ለማግኘት እየተሰራ ያለውን ተግባር አድንቀዋል::

የቡና ማሰልጠኛ ማዕከሉም በአራት የቡና ዘርፎች ማለትም በቡና ቅምሻ፣ በዘመናዊ የቡና አቆላል፣ በባሬስታ እና በኤክስፖርት ዶክመንት አያያዝ ላይ በንድፈ ሐሳብና  በተግባር  በሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ  ባለስልጣን  ዋና ዳይሬክተር   አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በበኩላቸው በእውቀትና በክህሎት የዳበረ የሰው ኃይል ለቡናው ኢንዱስትሪ በማበርከት ረገድ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ፒያሳ በሚገኘው   በተለይም አነስተኛ እና መካከለኛ አምራቾችን በገበያ፣ በፈጠራና በምርት ዲዛይን UNIDO ድጋፍ የሚደረግባቸው ምርቶች ማሳያ  በCreative hub ጉብኝት ተደርጓል::

በዚህ የፈጠራ ማዕከል የሚገኙ በአነስተኛ እና መካከለኛ ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾች መንግስት  የመስሪያ ቦታ  ድጋፍ እንዳደረገላቸውና UNIDO ም በገበያ እና  በልዩ ፈጠራ ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሆነ  በመግለጽ  በቀጣይ ጥራት ያላቸው   ምርቶችን ለአለም ገበያ  በማቅረብ ተወዳዳሪ ለመሆን  የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ገልጸዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments