በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኙ አምራች...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ጉብኝት ተካሄደ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር አቶ መላኩ አለበል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ፣አስተባባሪ ኮሚቴዎች እና ከፍተኛ የስራ አመራሮች በተገኙበት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ በሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ጉብኝት  ተካሂዷል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚንስትር ክቡር አቶ መላኩ አለበል ባለፉት አራት አመታት የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም በየአመቱ እየጨመረ እንደሆነ ገልጸው እንደ አዲስ አበባ ከተማ  የማምረት አቅም  ከሀገራዊ  አማካኝ የማምረት አቅም በላይ እንደሆነ ገልጸዋል።

ይህ እንደ ከተማ የታየው ከፍተኛ የማምረት አቅም የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት  በመሰረተ ልማት፣በገበያ ትስስር፣ በብድር አቅርቦት፣በመስሪያ ቦታ አቅርቦት እና በሌሎችም ለዘርፉ  ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።

በቀጣይ ሚኒስቴር መ/ቤቱም አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚገጥማቸውን ተግዳሮት በመለየት  ለመፍታት ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አቶ መላኩ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ  ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው ጉብኝቱ በዋናነት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በአምራቾች ላይ ያመጣውን ለውጥ ለማየት እና አምራቾች የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች በመለየት ለሚመለከተቻው የስራ ኃላፊዎች ለማሳወቅ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በጉብኝቱም የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከማሳደግ በተጨማሪ በአነስተኛ ቦታ ከፍተኛ የስራ እድል መፍጠር እንደቻሉ ገልጸው ተጨማሪ ድጋፍ ቢደረግቸው የበለጠ የስራ እድል በመፍጠር፣ምርት ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት እና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ገልጸዋል፡፡

አቶ ጃጥራር አክለውም በቀጣይም በኢንዱስትሪዎች ላይ ተመሳሳይ ጉብኝት በማድረግ ችግራቸውን ከፈታን ተስፋ ያላት ሀገር እና ከተማ በመፍጠር አብዛኛውን ፍጆታ በራስ አቅም የመሸፈን አቅም እንዳለ  ገልጸዋል፡፡

ኢንዱስትሪ የሀገር ሀብት ነው ያሉት ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አምራቾች በስራ እድል ፈጠራ፣በገበያ ማረጋጋት፣የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት፣ተኪ ምርት በማምረት፣ ሚናቸው ከፍተኛ በመሆኑ የስራ ኃላፊዎች ይህን አምራች ዘርፍ በመደገፍ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments