"በመዲናዋ ከነዳጅ ስርጭትና ግብይት ጋር የሚስተ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

"በመዲናዋ ከነዳጅ ስርጭትና ግብይት ጋር የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በቅንጅት እየተሠራ ነው" ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ

በነዳጅ አቅርቦት  እና ፍትሀዊ  ስርጭት  ላይ የሚመለከታቸው  የስራ ኃላፊዎች፣ የጸጥታ አካላት ኃላፊዎች፣የህገወጥ ንግድ ቁጥጥር ገበያ ማረጋጋት እና ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ግብረ ሀይል አባላት፣ ባለድርሻ አካላት እና የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ በመዲናዋ ከነዳጅ ስርጭትና ግብይት ጋር የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በቅንጅት እየተሠራ  እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

እንደሀገር ያለውን የኢኮኖሚ እድገት መሰረት ያደረገ የነዳጅ አቅርቦት ቢኖርም  በከተማዋ የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎች በህጋዊ ስርዓት ለተጠቃሚዎች ከማቅረብ አኳያ በአንዳንድ ማደያዎች ክፍተቶች መኖራቸውንም ገልፀዋል።

ከሚታዩ ችግሮች መካከል የወሩ መጨረሻ አካባቢ በማደያዎች በቂ የነዳጅ ክምችት እያለ ለተሽከርካሪዎች የለም በማለት የሚመልሱ መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በአንዳንድ ማደያዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እየሰራ እንደሆነና   አጥፊዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው በቀጣይም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የተጠናከረ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ነዳጅን በሕገወጥ መንገድ በመሸጥ ነዋሪውን ለምሬት የሚዳርጉ፣ ገበያው እንዳይረጋጋ እና በትራፊክ እንቅስቃሴ ላይ ጫና የሚፈጥሩ ነጋዴዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዓባይ አሳስበዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments