"ከተማ አስተዳደሩ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ አዎን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

"ከተማ አስተዳደሩ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ አዎንታዊ ድርሻ ላላቸው አምራቾች  ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ነው" ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ይገኛል፡፡

በተለይም ባለፉት የለውጥ አመታት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት የመስሪያ እና ማስፋፊያ ቦታ፣ የመስሪያ መሬት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች በማቅረብ የአምራቾችን ምርትና ምርታማነት እያሳደረገ ይገኛል፡፡

በዛሬው እለትም  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የካቢኒ ውሳኔ ባገኙ አገራዊ ፋይዳ ባላቸው ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ እቅድ ላይ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች እና አስፈጻሚ መ/ቤቶች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ  ከተማ አስተዳደሩ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ በተለይም በኢኮኖሚ ግንባታ፣በውጭ ምንዛሬ፣በስራ እድል ፈጠራ እና ገቢ ምርት በመተካት አዎንታዊ ድርሻ ላላቸው አምራቾች  ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪው የመሬት ፍላጎት ብዙ ቢሆንም ከተማ አስተዳደሩ የሚችለውን እያደረገ እንደሆነ ገልጸው በቀጣይም አልሚዎች ሁሉንም ከመንግስት ብቻ ከመጠበቅ ወጥተው በራሳቸው ጥረት መስራት እንደሚገባቸው አቶ ጃንጥራር አሳስበዋል፡፡ 

ከዚህ በፊት መሬት ወስደው አጥረው የተቀመጡና ስራ ያልጀመሩ አምራቾች እንዳሉ የገለጹት ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር በቀጣይ ከዚህ በፊት የመስሪያ መሬት የወሰዱም ሆኑ አዲስ የሚወስዱ አምራቾች  በፍጥነት ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ መኮነን ያዒ በበኩላቸው ውይይቱ በዋናነት መሬት ወስደው ወደ ልማት የሚገቡ አምራቾች በተፈቀደላቸው መሬት ላይ በቶሎ ወደ ልማት እንዲገቡ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነ ገልጸው አምራች ኢንዱስትሪዎችም በሚወስዱት መሬት ላይ ተገቢውን ልማት በማልማት ምርተማነታቸውን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments