በተኪ ምርትና በወጪ ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ሴት አምራቾች ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት የራሳቸውን አሻራ እያሳረፉ እንደሆነ ተገለጸ።
በአገር በቀል አምራች ኢንዱስትሪዎችና የወጪ ንግድ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች ውጤታማ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሚገኙ የአለምነሽ ጌታቸው አስመጭና ላኪ አምራች ተጨባጭ ማሳያ ነው።
አምራቹ በዓይነት በርከት ያሉ የባልትና ውጤቶችን ወደ ውጭ አገራት በመላክ ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
የአለምነሽ ጌታቸው አስመጭና ላኪ ከወጪ ንግድ ዘርፉ ባሻገር በተኪ ምርት ዝግጅት ላይም በስፋት እየተሳተፈ ሲሆን በተለይም የጨረቃ ጨርቅ ግብዓቶችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባትና ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሬን ለማዳን የሚያስችል ተግባር እያከናወነ ይገኛል።
አምራቿ እንደተናገሩት ከሆነ ለተመዘገበው ውጤት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ እያደረገ ያለው ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትል ትልቅ ድርሻ አለው።
ቢሮው በሥራ ሂደት ውስጥ የሚገጥሙ የመሠረተ ልማት ማነቆዎችን በመለየትና ፈጣን መፍትሄዎችን በመስጠት ረገድ እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት አምራቾች በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራ እንዲገቡ አስችሏቸዋል።
በመሆኑም አምራቹ ከቢሮው የሚደረግለትን ይህንኑ ድጋፍ በመጠቀም የምርት አቅሙን በማሳደግና የተለያዩ መሰናክሎችን በመሻገር ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። ይህ የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ በመዲናዋ ያለውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍም የራሱን ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
አምርቹ ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ውጤታማ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን ይህም ለዜጎች የገቢ ምንጭ ከመሆን ባለፈ ለአከተማዋ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት የራሱን አሻራ እንዲሳርፍ አድርጎታል።
በአጠቃላይ የአለምነሽ ጌታቸው አስመጭና ላኪ ድርጅት በወጪ ንግድ፣ በተኪ ምርትና በሥራ ዕድል ፈጠራ ረገድ እያከናወነ ያለው ተግባር ለሌሎች አምራቾችም አርአያ ሊሆን የሚችልና የአገር ውስጥ ምርትን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments