የረመዳን እና የኢድ በአል አቅርቦት የነበሩ ጥን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

የረመዳን እና የኢድ በአል አቅርቦት የነበሩ ጥንካሬዎች እና የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም ለመጭው ተንሳኤ በአል እቅድ ዝግጅት መደረጉ በዝርዝር ተገመገመ።

 የገበያ ማረጋጋት፣ ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር እና “ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት” ግብረ ሀይል በኢድ አልፈጥር በዓልን የተረጋጋ ግብይት እንዲካሄድ የተሰሩ ስራዎችን  እና በመጪው የፋሲካ በዓል የምርት  የአቅርቦት እጥረትና ያልተገባ የዋጋ ጭማሬ እንዳይኖር እንዲሁም ህገወጥነትን ለመከላከል የሚሰሩ ስራዎችን ገምግሟል ።

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ የተከበሩ  አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት፣  በኢድ አልፈጥር በአል አቅርቦቱን ከፍ ለማድረግ የተሰራው ስራ አበረታች መሆኑን ገልጸው  ከፊታችን የሚከበረውን የፋሲካ በዓል  ምክንያት በማድረግ የምርት እጥረትና ያልተገባ የዋጋ ጭማሬ እንዳይኖር  አመራሩ በትኩረት ይሰራል ብለዋል ።

የግብረ ሀይሉ አባላት በበኩላቸው የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር ከክልሎች ጋር ትስስር በመፍጠርና  ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይፈጠር  ከደላላ ነጻ የሆነ ግብይት እንዲኖር በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

 በመጨረሻም በመጪውን የፋሲካ በዓል የተረጋጋ ግብይት እንዲከናወን የአቅርቦት  እጥረት እንዳይፈጠርና ህገወጥነትን ለመከላከል ችግር ፈቺ ተጨባጭ እቅድ ማቀድ፣ አቅርቦትን ማረጋገጥ፣ ቦታዎችን ማዘጋጀት፣ አቅርቦትን የሚያሳልጥ ቁጥጥር ማድረግ እንዲሁም  የግብይት ማእከላት ላይ ደላላ እንዳይኖር በመከታተል በትኩረት እንዲሰሩ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ አሳስበዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments