በመስሪያ ቦታዎች ላይ የሚፈጠርን ህገወጥ አሰራር...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

በመስሪያ ቦታዎች ላይ የሚፈጠርን ህገወጥ አሰራር ለመከላከል በቅንጅት በመስራት ተጨባጭ መረጃ መያዝ እንደሚገባ  ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ለማሳደግ  ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የመስሪያና የማስፋፊያ ቦታ  እያቀረበ ይገኛል።

ቢሮው  ከማዕከል እና ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ጸ/ቤት ኃላፊዎች እና  ከመስሪያ ቦታዎች ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ  እና የክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች  ጋር ዉይይት አካሂዷል፡፡  በውይይቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ  መንግስት የአምራች ዘርፉን ለማበረታታት   ትኩረት በመስጠት ድጋፍና ክትትል እያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል። በመስሪያ ቦታዎች ላይ የሚፈጠርን ህገወጥ አሰራር ለመከላከል በቅንጅት በመስራት ተጨባጭ መረጃ መያዝ እንደሚገባ  ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አሳስበዋል።

የተሻሉ አምራቾችን በሚያበረታታ መንገድ በትክክል የማይሰሩትን በመለየት  ውጤታማ ስራ ለሚሰሩ  አምራቾች በማስተላለፍ  ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባም ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል።

በቀጣይም የአምራቾችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጋራ ጥናት  እንደሚካሄድም አቶ ጃንጥራር ገልጸዋል። መንግስት ባመቻቸላቸው የመስሪያ ቦታ  ከዘርፍ ውጭ ከተሰራበት፣ ውጤታማ አምራች ካልሆነ፣ እንዲሁም ህገወጥ ስራ የሚሰራበት ከሆነ   ህጋዊ እና ውጤታማ ስራ ለሚሰራ አምራች እንደሚተላለፍ  ገልጸዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments