"መንግስት የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና ገበያውን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

"መንግስት የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና ገበያውን ለማረጋጋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ  ነው" ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ

የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና ገበያውን ለማረጋጋት የኢንዱስትሪ ምርቶች፣ የእንስሳት ተዋጽኦና የግብርና ምርቶች በህብረት ስራ ማህበራት በኩል በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲደርሱ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ ገልጸዋል።

 በልደታ ክፍለ ከተማ አዲስ ሚሊኒየም ሸማች ህብረት ስራ ማህበር አንዱ ማሳያ መሆኑን ገልጸው እንደዚህ አይነት የአቅርቦት ስራዎች በበዓላት ብቻ ሳይሆን  የሁልጊዜ ተግባር በማድረግ አመራሩ በትኩረት እንዲሰራ ምክትል ከንቲባው አሳስበዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ  በበኩላቸው ህብረት ስራ ማህበራት ከአምራቾች ምርቶችን በቀጥታ በመቀበል  ለተጠቃሚዎች እንዲያቀርቡ እየተሰራ  መሆኑን ገልጸዋል።

የኑሩ ውድነትን ለመቀነስና ገበያን  ለማረጋጋት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ባዛሩ  ተከፍቷል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments