ሰው የሚሰጠው ተርፎት ብቻ ሳይሆን ካለው ላይ በመቀነስ ነው" - ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ
የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ባለሀብቶችን በማስተባበር በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ያስገነባቸውን የመኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች አስተላለፈ።
በዕለቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ከተማ አስተዳደሩ ለቤት ልማት ከፍተኛ ሀብት በመመደብ በቤት ልማት ከፍተኛ ስራ መስራቱን ገልጸዋል።
በተለይ ባለፉት የለውጥ አመታት ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ቤቶችን በማልማት ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍን ጠቁመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስተራችን በጀመሩት ከተማን መልሶ በማልማት የማደስ ስራ ቀና ልብ ያላቸውን ባለሀብቶች በማስተባበር ከፍ ሲል ህንጻ ዝቅ ሲል ቪላ የሆኑ ቤቶችን በመገንባት ተጠቃሚዎች ህይወታቸውን በደስታ እንዲያሳልፉ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እንደተሰሩም ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል።
ሰው ተርፎት ብቻ ሳይሆን የሚሰጠው ካለው ላይ በመቀነስ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ሁሉም መረዳዳት ቢችል ችግሮችን መቅረፍ ይቻላል ብለዋል።
መጨረሻም በዚህ የቤት ግንባታ የተሳተፉት ዮት ኮንስትራክሽን እና ግንባታውን ሲከታተሉ ለበሩ ለኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አመራሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮችን በማመስገን ለቤት ተጠቃሚዎችም እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments