ገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሀገር ኢኮኖሚ እድ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

ገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ትልቅ አሻራ መሆኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ እና  የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮችና ሰራተኞች በቅርቡ ተመርቆ ሥራ የጀመረውን የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ፓርኩ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት፣ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር እንዲሁም ሀገሪቱን በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የሚያደርግ ለትውልድ የሚተላለፍ አሻራ መሆኑን ተገልጿል።

ፓርኩ ለ20,000 ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር ሲሆን 4 ኪሎ ሜትር አስፋልት መንገድ የተሰራለት እና የመብራት መቆራረጥን ለመከላከል ጄኔሬተር እንዲሁም የውሃ ጉድጓድ የተሟላለት ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ፓርክ ነው፡፡

መንግስት አምራች ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ቀዳሚ ስፍራ እንደሚይዝ የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይም ተኪ ምርትና ለኤክስፖርት የሚውሉ ምርቶችን የሚያመርቱ የሀገር ውስጥ አምራቾች ተጠቃሚ ሆናዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments