የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የንግድ፣ኢንዱስት...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የንግድ፣ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመስክ ምልከታ አደረጉ።

በምልከታውም በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚገኙ ምርት ወደ ውጭ የሚልኩ እና ተኪ ምርት  አምራች ኢንዱስትሪዎች ያሉበት ደረጃ ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ በአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የምክትል ከንቲባ አማካሪ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር ለቋሚ ኮሚቴው አባላት በሰጡት ማብራሪያ፣ ከተማ አስተዳደሩ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ገልጸው የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮም  የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ለማሳደግ  ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር፣ የመሠረተ ልማት በማሟላት እና የገበያ ትስስር በመፍጠር ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች ያጋጠሟቸውን የማኑፋክቸሪንግ ማነቆዎች፣ የፋይናንስ እና የሎጂስቲክስ ጥያቄዎችን ለመፍታት ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑም ተገልጿል።

የምክር ቤቱ የኢንዱስትሪ፣ ንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በፓርኩ ውስጥ ያለውን ከፍተኛ የምርት እንቅስቃሴና ለበርካታ ዜጎች የተፈጠረውን የስራ ዕድል ከተመለከቱ በኋላ፤ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አምራቾችን ለመደገፍና የአገር ውስጥ ምርትን ለመተካት እያደረገ ያለውን የተጠናከረ ክትትል አድንቀዋል።

በጉብኝቱ ማጠቃለያ ይህ የጋር ጉብኝት በከተማዋ የኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚን ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ መሆኑም ተገልጿል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments