"የሀገሪቱን እድገት ለማረጋገጥ ከገጣጣሚነት ወደ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

"የሀገሪቱን እድገት ለማረጋገጥ ከገጣጣሚነት ወደ አምራችነት መሸጋገር አለብን"ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ

‎በአዲስ አበባ ከተማ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት ከሰኔ 10-14 በመስቀል አደባባይ የተዘጋጀውን የአዲስ አውቶሞቲቭ ኤክስፖ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በይፋ ከፍተዋል።

‎አቶ ጃንጥራር በመክፈቻው ስነ-ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እንዲህ አይነት አምራቾችንና አስመጭዎችን የሚያሳትፉ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀቱ የግሉ ዘርፍ ራሱን በራሱ እንዲመራና በከተማዋ ኢኮኖሚ ውስጥ የጎላ ሚና እንዲጫወት እንደሚያስችለው ገልጸዋል።

‎ኃላፊው አክለውም መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸውና ቅድሚያ ካስቀመጣቸው የልማት መስኮች መካከል ኢንዱስትሪ አንደኛው መሆኑን አስገንዝበዋል። እንደ ቴክኖሎጂ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና ግብርና ሁሉ በኢንዱስትሪው ውስጥም ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቷል።

‎ሀገሪቱ ወደኋላ የቀረችበት ዋናው ምክንያት በኢንዱስትሪው ዘርፍ ያላት አቅም ዝቅተኛ በመሆኑ እንደሆነ የገለጹት አቶ ጃንጥራር፣ ይህንን ለማሻሻል መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በተለይም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን ግዙፍ የህዝብ ቁጥርና ሰፊ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ አምራችነትን ማሳደግና ከአለም አቀፍ እድገት ጋር ተወዳዳሪ መሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

‎ኤክስፖው ምርትን ከማስተዋወቅ ባለፈ ምርቶችን በገበያ ላይ በቀላሉ ለመሸጥ ሰፊ እድል እንደሚፈጥር የተናገሩት ምክትል ከንቲባው፣ አዲስ አበባ ለአፍሪካና ለአለም እንደ መግቢያ በር የምታገለግል መሆኗ ለዘርፉ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን አብራርተዋል።

‎በመጨረሻም አቶ ጃንጥራር በኤክስፖው ላይ የቀረቡትን በተለይም በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማድነቅ፣ በወቅታዊ ሁኔታዎች ምክንያት የነዳጅ እጥረት በሚያጋጥምበት ወቅት ከተማዋንና ሀገሪቱን ካለችበት የነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ማብዛት ወሳኝና የጊዜው ጥያቄ መሆኑን ገልጸዋል።

‎ሀገሪቱ በታዳሽ ሃይል የታደለች በመሆኗ ይህንን አቅም በመጠቀም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር ማሳደግ እንደሚገባ ጠቁመው፣ አምራቾች የመለዋወጫ እቃዎችን ጭምር እዚሁ ሀገር ውስጥ ማምረት የሚችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments