የምርት አቅርቦትን በማሳደግ የዋጋ ንረትን ለመቀ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

የምርት አቅርቦትን በማሳደግ የዋጋ ንረትን ለመቀነስ ግብረ ሀይሉ በትኩረት ሊሰራ ይገባል፤ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ

የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር የክትትልና የቁጥጥር ሥራዎችን በማጠናከር በቀጣይ አራት  ወራት በሚሰሩ ስራዎች እቅድ ላይ የግብረ ሀይሉ አባለላትና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት ተደርጓል።

 

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና ገበያውን ለማረጋጋት ለግብረ ሀይሉ  በተሰጠው አመራር አበረታች  ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።

 

አቶ ጃንጥራር አክለውም ግብረ ሀይሉ በእቅዱ ላይ ግልጽ ግንዛቤ በመያዝ የህብረተሰቡን ጥያቄ በአግባቡ መመለስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

 

የቀጣዩ የአራት  ወራት እቅድ ዋና ትኩረት የሰብል ምርት አቅርቦትን በማሳደግ የዋጋ ንረትን መቀነስ፣ የሰንበት ገበያ መዳረሻዎችን በስታንዳርድ መሰረት ማስፋት፣ የኢንዱስትሪ ምርቶች አቅርቦትን ማሳደግ እንዲሁም የንግድ ቁጥጥርን በማጠናከር የገበያ ዋጋን ማረጋጋት መሆኑ ተገልጿል።

 

ተሳታፊዎች በበኩላቸው፣ ግብረ ሀይሉ በየወቅቱ የሚለዋወጠውን የገበያ ሁኔታ መሰረት ያደረገ እቅድ በማዘጋጀትና በመተግበር ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

 በቀጣይም ህገወጥ የግብይት ስርዓት እንዲኖር ያለንግድ ፍቃድ፣ በተሰረዘ ንግድ ፍቃድ፣ባልታደሰ፣ ያለደረሰኝ እንዲሁም ያለዘርፍ የሚሰሩትን በመለየት  የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የቅንጅት ስራዎችን በማጠናከር ግብረ ሀይሉ   በትኩረት እንዲሰራ ተጠቁሟል።

አቶ ጃንጥራር አባይ በማጠቃለያቸው፣ በቀጣይ ወራት ሁሉም ግብረ ሀይል እቅዱን በመውሰድ  የምርት አቅርቦትን በማሳደግ የገበያ ዋጋን ማረጋጋት የግብረ ሀይሉ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ገልጸው፣ አቅርቦትን ማሳደግና መምራት፣ ህግን ማስከበር እና ተጠያቂነትን መፍጠር እንዲሁም ተዓማኒ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ሁሉም አካላት ኃላፊነትን  በመወጣት ለተሻለ ውጤት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

 


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments