
አምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ ምርት እንዲያመርቱ እውነተኛና ተጨባጭ የሆነ ድጋፍና ክትትል እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡
አምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ ምርት እንዲያመርቱ እውነተኛና ተጨባጭ የሆነ ድጋፍና ክትትል እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡
ቢሮው በሚያዝያ ወር ለሚካሄደው ኢግዚቢሽንና ባዛር ላይ ለሚሳተፉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር በምርት ጥራት እና አቅርቦት እንዲሁም በኢግዚቢሽንና ባዛሩ ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት መድረክ አካሄዱ፡፡ በውይይቱም ላይ ከኢንዱስትሪዎች በርካታ መፍትሔ የሚሹ ሃሳቦች ተነስተዋል፡፡ ከተነሱት ሃሳቦች መካከል የመስሪያ ቦታ ማስፋፊያ ችግር፣መሠረተ ልማት ችግር፣የገበያ ትስስር የመሳሰሉት ችግሮች መፍትሔ እንዲሰጣቸው ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በውይይቱ ማብራሪያ የሰጡት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የፋሲሊቴሽንና ካይዘን ትግበራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ግዛው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መሠረታዊ ዓላማ የኢንዱስትሪ ሴክተሩ እና አምራች ኢንዱስትሪዎች በኢኮኖሚው ውስጥ ያላቸው ድርሻ በጥራትና በምርት አቅርቦት ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል እንደሆነ ገለጸዋል፡፡
አቶ ኤፍሬም አክለዉም በዓለማችን ላይ ያደጉ ሀገሮች ዋነኛው ሚስጢር የኢንዱስትሪ ሪቮሊሽን ላይ ያደረጓቸው ተጨባጭ ለውጦች መሆናቸውን ጠቅሰዋል ይህን ለውጥ በሀገራችን ለማስመዝገብ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍና መሠረተ ልማቶችን በማሟላት ችግሮችን በመቅረፍ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ተኪ ምርት እንዲያመርቱ ማስቻል ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም አቶ ኤፍሬም ኢንዱስትሪዎች የሚገጥማቸዉን የብድር አቅርቦት ችግር፣ የመስሪያ ቦታ እጥረት እና የገቢያ ትስስር ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ ባያገኙም በጊዜ ሂደት ከሚመለከተው አካል ጋር በቅንጅት በመስራት በዘላቂነት ለመፍታት ጊዜ የማንሰጠው ሥራችን ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ሚያዝያ07/2016 ዓ.ም
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments