
አምራች ኢንዱስትሪዎች ጥራት ያለውና በቂ ምርት እንዲያመርቱ መደገፍ እና መከታተል እንደሚገባው ተገለጸ።
አምራች ኢንዱስትሪዎች ጥራት ያለውና በቂ ምርት እንዲያመርቱ መደገፍ እና መከታተል እንደሚገባው ተገለጸ።
የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች እና የክፍለ ከተማ የሥራ አስተባባሪዎች በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የልምድ ልውውጥና ጉብኝት አደረጉ።
በጉብኝቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማዕረግ ግርማይ ይህ ልምድ ልውውጥ እና ጉብኝት ዋናው አላማ ከጉብኝትና ከልምድ ልውውጥ ባለፈ ዕውቀትና ልምድ አግኝተንበት ኢንዱስትሪዎች ችግር ፈችና ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ሥራችን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከማድረገግ በተጨማሪ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ያስችለናል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
እንደ ሀገር ኢንዱስትሪ መር ሥራዎች እያደጉና ምርትና ምርታማነት ውጤታማነት እድገት እያሳየ በመምጣቱ የድጋፍና ክትትል ሥራችን ዘመኑ በደረሰበት ደረጃ የሰው ኃይልና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ሥራታችን ላቅ ያለ ሊሆን ይገባል ሲሉ አቶ ማረግ ገልጸዋል።
በመጨረሻም በቅንጅት በመስራት ኢንዱስትሪዎቻችን ውጤታማ ምርት እና ተኪ ምርቶችን አምርተው ለገቢያ በማቅረብ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና የውጭ ምንዛሬን እንዲያስቀሩ ማስቻል አለብን ያሉት አቶ ማዕረግ በቂ ምርት እና ጥራትንም የጠበቀ ምርት እንዲመረት የድጋፍና ክትትል ሥራችን ተጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል።
ሚያዚያ 5/2016 ዓ.ም
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments