የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ለማሳደግ...

image description
- In Uncategorized    0

የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ለማሳደግ ተገቢዉን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ለማሳደግ ተገቢዉን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በአነስተኛ፣በመካከለኛ እና በከፍተኛ ደረጃ የሚገኙ በርካታ አምራች ኢንዱስትሪዎች አሉ፡፡ እነዚህ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና ማርታማነትን በማሳደግ፣በስራ እድል ፈጠራ እና ተኪ ምርት በማምረት ከፍተኛ ድርሻ አላቻዉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮም ባለፉት 9ወራት የተሰሩ ተግባራትን አፈጻጸም በተመለከተ ከቢሮዉ የዘርፍ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ጋር ገምግሟል፡፡ ባለፉት 9ወራት አምራች ኢንዱስትሪዎች የነበረባቸዉን የመሰረተ ልማት ችግር መፍታት እንደተቻለና ለ403 አምራች ኢንዱስትሪዎች ዘመናዊ ሀይል ቆጣቢ ቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ ማድረግ እንደተቻለ በሪፖቱ ቀርቧል፡፡

በሀገር ዉስጥና ከሀገር ዉጭ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የገበያ ትስስር በመፍጠር የተቻለ ሲሆን ወደዉጭ ከሚልኩ ኢንዱስትሪዎች ከ67 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ እንደተገኘም በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም 247 ገቢ ምርት የሚያመርቱ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ማፍራት የእንደተቻለና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደዉጭ ምርታቸዉን እንዲልኩ ማድረግ እንደተቻለም ተግልጿል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ የዘርፉ ባለሙያዎችና አመራሮች ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ተገቢዉን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸዉ ገልጸዉ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግም የገበያ ትስስር መፍጠር እና ብድር ማመቻቸት እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡ አቶ ጃንጥራር አክለዉም በቀጣይም በየዘርፉ ታቅደዉ ያልተከናወኑ ተግባራትን በመለየት መስራት፣ ኢንዱትሪዎች የሚገጥማቸዉን ችግር በመለየት መፍታት እና የኢንዱስትሪዎችን መረጃ ማጥራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ሚያዚያ 3፣2016 ዓ.ም


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments