ለሀገር የኢኮኖሚ ግንባታ የአምራች ኢንዱትሪው ሚ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

ለሀገር የኢኮኖሚ ግንባታ የአምራች ኢንዱትሪው ሚና የማይተካ ነው፤

ለሀገር የኢኮኖሚ ግንባታ የአምራች ኢንዱትሪው ሚና የማይተካ ነው፤

ከቡር አቶ ጃንጥራር አባይ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ

ቢሮው አምራች ኢንዱትሪዎች ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እና ከመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ምክክር አድርጓል፡፡

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ጃንጥራ አባይ እንደገለጹት ለኢኮኖሚው ግንባታ እና ቋሚ የስራ እድል በመፍጠር አምራች ኢንዱትሪዎች ሚናቸው ከፍተኛ በመሆኑ የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች መፍታት የባለድርሻ አካላት ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

ቢሮው የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የአቅም ግንባታ ስልጠና፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን መፍታት፣ የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ ማመቻቸት፣ የመሳሪያ ሊዝ እንዲሁም የግብዓትና የገበያ ትስስር እንዲያገኙ መሰራቱን በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የፋሲሊቴሽንና የካይዘን ትግበራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ኤፍሬም ግዛው ጠቁመው አመርቂ ውጤትም ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

ዶክተር ኤፍሬም አያይዘውም ባለድረሻ አካላት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ጥያቄ የሚሰጡት ምላሽ አነስተኛ መሆን፣ የተጠናከረ የቅንጅት ስራ አለመኖር፣ የመረጃ ጥራትና ተናባቢነት ችግር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያጋጠሙ ችገሮች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት በበኩላቸው በአምራች ኢንዱስትሪዎች የቀረቡና በቢሮው የተረጋገጡ ችግሮችን አሰራሩን ጠብቀው ምላሽ ለመስጠትና አምራች ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አቅም በመለየት ችግሮቻቸውን በመፍታት ምርትና ምርታማነታቸውን ማሳደግ ከመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት ባለፈ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የሚሻ በመሆኑ በቀሪ ወራቶች በየደረጃው ያለው አመራር የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ችግር በባለቤትነት እንዲፈቱና ተባባሪ አንዲሆኑ የተከበሩ አቶ ጀንጥራር አባይ አሳስበዋል፡፡

ሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments