





ቢሮው ከዘርፉ አመረሮች፣ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ጋር በዲጅታል (Smart Office) ትግበራ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የሚሰጣቸዉን አገልግሎቶች ይበልጥ ለማሳለጥና ከወረቀት የጸዳ ለማድረግ የዲጅታል (Smart Office) ትግበራ ለማስጀምር እየሰራ ይገኛል፡፡
በዚህም አተገባበሩን በሚመለከት ከቢሮዉ የዘርፉ አመረሮች፣ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ጋር በዲጅታል (Smart Office) ትግበራ ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በዉይይቱ የተገኙት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማዕረግ ግርማይ የዲጅታል (Smart Office) ትግበራ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጅና አሰራርን በመጠቀም አስተማማኝ እና ወጪ ቆጣቢ ከወረቀት የፀዳ ጠንካራ Smart Office ትግበራ በማልማት በቀላሉ በየትኛውም ቦታ በቀላሉ ሊተገበር የሚችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አቶ ማዕረግ አክለዉም የዲጅታል (Smart Office) ትግበራው ለቢሮው ደንበኞች፣ አመራር እና ሰራተኞች መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ እድሎችን እንደሚሰጥም ገልጸዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments