



ድህነትንና ስራ አጥነትን ለመቀነስ የአምራች ኢንዱስትረዎችን ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
ቢሮዉ ከክፍለ ከተማ የዘርፉ አመራሮች ጋር በበጀት አመቱ እቅድ አፈጻጸም ላይ ዉይይት አካሂዷል፡፡ የበጀት ዓመቱ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡
በበጀት አመቱ አምራች ኢንዱስትሪዎቸ ምርታቸዉን ወደዉጭ በመላክ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ ማስገኘት እንደተቻለ በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡ በተያያዘም ኢንዱስትሪዎች የገጠማቸዉን የመሰረተ ልማት ችግር መቅረፍ እንደተቻለና ተኪ ምርት በማምረት፣በስራ እድል ፈጠራ፣የዉጭ ምንዛሬ በማስገኘት በኩል በሁሉም ክፍለ ከተሞች የተሻለ ስራ እንደተሰራ ተገልጿል፡፡
ድህነትንና ስራ አጥነትን ለመቀነስ የአምራች ኢንዱስትረዎች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ተገቢዉን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡
በዉይይቱ የተገኙት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአምራች ኢንዱስትሪ ድጋፍ ዘረፍ ኃላፊ አቶ ማዕረግ ግርማይ በበጀት ዓመቱ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ማሳደግ እንደተቻለ በመግለጽ በቀጣይም ኢንዱስትሪዎች በስራ እድል ፈጠራ፣በምርታማነት እና ተኪ ምርት በማምረት ላይ አቅማቸዉን ለማሻሻል በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የፋሲሊቴሽን እና ካይዘን ትግበራ ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ኤፍሬም ግዛዉ በበኩላቸዉ በበጀት ዓመቱ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ የሚያስችል መመሪያዎችን በማዘጋጀት ወደስራ መግባታችን ስራዉን ዉጤታማ እንዳደረገላቸዉ ገልጸዉ የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ለማሻሻል በየደረጃዉ ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገቢዉን ድጋፍና ክትተትል ማድረግ እንደሚገባቸዉ ገልጸዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments