በበጀት ዓመቱ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ከ57 በመቶ ወደ 61 በመቶ ከፍ ማድረግ መቻሉ ተገለጸ፡፡
በኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በአምራች ኢንዱስትሪ ድጋፍ ዘርፍ የእንጨት ብረታ ብረትና ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት በበጀት ዓመቱ አፈጻጸም እና ትኩረት በሚሹ ቀጣይ ተግባራት ላይ ከማእከልና ከክ/ከተማ ዳይሬክተር፣ ቡድን መሪና ባለሙያዎች ጋር ውይይት እድርጓል፡፡
በበጀት ዓመቱ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የማሽነሪ ሊዝ አቅርቦት፣ የኢንዱትሪ ኤክስቴንሽን እንዲሁም የንግድ ልማት አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን የእንጨት ብረታ ብረትና ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ እሸቴ ተናግረዋል፡፡
በተደረገላቸው ድጋፍም የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከ57 በመቶ ወደ 61 በመቶ ከፍ ማለቱን አቶ ሀብታሙ ጠቁመዋል፡፡
ኢንዱትሪዎችን መደገፍና ችግራቸውን መፍታት ለሀገር እድገት አወንታዊ አበርክቶ ስላለው የአምራች ኢንዱስትሪዎችን መረጃ ማጠናከር፣ በእድገት ደረጃቸው፣ በቴክኖሎጂ አቅማቸውና በምርት ጥራት ስታንዳርድ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ ሞዴል ኢንዱስትሪዎችን መለየትና ተሞክሯቸውን ማስፋት እንዲሁም የሚያጋጥማቸውን የአሰራር ችግር በመለየት መፍትሄ ማስቀመጥ በቀጣይ በትኩረት ሊሰራ አንደሚገባ አቶ ሃብታሙ ጠቀሙዋል፡፡
በመጨረሻም እቅድ ሲታቀድ በእውቀት ላይ መመስረትና የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ቁጥር መሰረት ማድረግ እንደሚገባ አቶ ሀብታሙ እሸቴ ተናግረዋል፡፡
ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments