








በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኢንዱስትሪዎች የነበረባቸዉን ችግር መቅረፍ ተችሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ዉይይት አካሄደ፡፡
በመድረኩም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ የቢሮዉ አመራሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም የክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና አስተባባሪዎች ተገኝተዋል፡፡
የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ዉይይት ተካሄደ ሲሆን በበጀት አመቱ በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ እራሱን ችሎ በአዲስ ከተዋቀረ በርካታ ስራዎችን መስራት እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡
አቶ ጃንጥራር አክለዉም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪዎች የገቢያ ትስስርና የባዛር ተሳትፏችው በማሳደግ እና መሰረተ ልማት ችግሮችን በመፍታት የተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም በ2016 በጀት ዓመት የነበሩ ክፍተቶችን በማረም በተያዘዉ በጀት ዓመት በጋራ በመስራት የተሻለ ዉጤት ለማምጣት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ላመጡ የቢሮዉ ዳይሬክቶሬቶች፣ቡድኖች ፣ባለሙያዎች እና ከፍለ ከተሞች እዉቅናና ሽልማት ተሠጥቷል፡፡
ሐምሌ 16፣2016 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃ
https://www.facebook.com/AACIDB
Telegram Adress
Website Address
https://www.industrydevelopment.gov.et
Youtube Adress
https://www.youtube.com/channel/UCfh4g0AVsFaHY2s0CnSRkjQ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments