




አምራች ኢንዱስትሪዎች በስራ እድል ፈጠራና በሀገር ኢኮኖሚ እድገት ሚናቸዉ ከፍተኛ ነዉ፡፡
ቢሮዉ ከአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር በምርት አቅርቦት ላይ ባሉ ችግሮች ዉይይት አካሂዷል፡፡
ዉይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራ አባይ አምራች ኢንዱስትሪዎች በስራ እድል ፈጠራና በሀገር ኢኮኖሚ እድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
አቶ ጃንጥራር አክለዉም አምራች ኢንዱስትሪዎች የዋጋ ንረትን በመከላከል ያላቸዉ ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዉ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች የዋጋ ንረትን በመከላከል በኩል ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚገባቸዉ አሳስበዋል፡፡
አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚገጥማቸዉን የመሰረተ ልማት፣የገበያ ትስስር፣የዉጭ ምንዛሬ እና የብድር አገልግሎት ችግር ለመፍታት ቢሮው አስፈላጊዉን ድጋፍ እንደሚደረግላቸዉ አቶ ጃንጥራር ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም አምራች ኢንዱስትሪዎች ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት የነበራቸዉ አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር የገለጹት አቶ ጃንጥራር አሁንም በእነዚህ በማህበራዊ ኃላፊነት ተሳትፎ ላይ የተለመደዉን አስተዋጽ እንድታበረክቱ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
አምራች ኢንዱስትሪዎች በበኩላቸዉ ቢሮዉ የሚጠበቅበትን ድጋፍና ክትትል እንዲያደርግላቸዉ ጠይቀዉ በሚከናወኑ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ የበኩላቸዉን ኃላፊነት እንደሚወጡ ገልጸዋል፡፡
ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም (ኢ.ል.ቢሮ)
ለተጨማሪ መረጃ
https://www.facebook.com/AACIDB
Telegram Adress
Website Address
https://www.industrydevelopment.gov.et
Youtube Adress
https://www.youtube.com/channel/UCfh4g0AVsFaHY2s0CnSRkjQ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments