የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የግብርና እና የኢንዱስ...

image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን አቅርቦት ማስፋት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የገቢ አሰባሰብን ለማሻሻልና የኑሮ ዉድነትን ለመቀነስ ከከተማ አስከ ወረዳ ካሉ የኑሮ ውድነትና ገበያ ማረጋጋት እና የገቢ ግብር አሰባሰብ ግብረ ሀይል ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

 

በመድረኩም ባለፉት ወራት በኑሮ ዉድነት ማረጋጋት እና ገቢ አሰባሰብ ላይ በተሰሩ ስራዎች ሪፖርት እና በቀጣይ ሶስት ወራት በሚሰሩ ተግባራት ላይ ዉይይት ተካሂዷል፡፡

በከተማዉ የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት ለመቀነስ በማህበራት በኩል የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች እየቀረቡ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

 

በቀጣይም አዲስ ዓመትን ታሳቢ በማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት አስፈላጊ ምርቶችን ለማቅረብ እየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

 

በውይይቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የግብረ ኃይሉ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ የገቢ አሰባሰብን ለማሳደግ እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የፓርቲ እና የገቢ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸዉ አሳስበዋል፡፡

 

በቀጣይም ለኑሮ ዉድነት ምክንያት የሆኑ ችግሮችን በመለየት የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርት አቅርቦትን ማሳዳግ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቶ ጃንጥራር ገልጸዋል፡፡

 

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ እና የግብረ ኃይሉ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ጀማሉ ጀንበር በበኩላቸዉ በማህበራት በኩል ለህብረተሰቡ የሚቀርቡ ምርቶችን ለማስፋት ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

 

ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም (ኢ.ል.ቢሮ)

ለተጨማሪ መረጃ

Facebook

https://www.facebook.com/AACIDB

Telegram Adress

https://t.me/AACIDB

Website Address

https://www.industrydevelopment.gov.et

Youtube Adress

https://www.youtube.com/channel/UCfh4g0AVsFaHY2s0CnSRkj


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments