
ችግኞችን መትከል የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ ወሳኝ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
"የምትተክል ሃገር፣ የሚያጸና ትውልድ!" በሚል መሪ ቃል የተጀመረዉ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ 20 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል እየተሰራ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮም ከሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጀመሮ በስሩ ከሚገኙ የክፍለ ከተማ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ከአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር በመተባበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም ሲያከናዉን ቆይቷል፡፡
በዛሬዉ ዕለትም የመጨራሻዉን ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች፣ከክፍለ ከተማ አመራሮች እንዲሁም በክፍለ ከተማዉ ከሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር አካሂዷል፡፡
በዕለቱም የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ቢሮዉ 40ሺ ችግኞች ለመትከል በማቀድ በተለያየ ቀናት ሁሉምን ክፍለ ከተሞች በማስተባበር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ሲያካሂድ እንደቆየ አስታዉሰዉ የሚተከሉ ችግኞች ፀድቀዉ ለወጣቶችና ለነዋሪዎች በተለይም የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ ለሚሰሩ ስራዎች ወሳኝ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡
አቶ ጃንጥራር አክለዉም ኢንዱስትሪዉን ለሚመሩ አመራሮች ብክለትን መቀነስ ዋና ስራ እንደሆነ ገልጸዉ ለዚህ ደግሞ ችግኞችን መትከል አስፈላጊ እንደሆነና የሚተከሉ ችግኞችን መንከባከብ እና መቆጣጠር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በዕለቱም 6,600 ችግኞች የተተከሉ ሲሆን በአጠቃላይ በሁሉም ዙሮች ከ40ሺ በላይ ችግኞችን በመትከል እቅዱን ማሳካት ተችሏል፡፡
ሐምሌ 23፣ 2016 ዓ.ም(ኢ.ል.ቢሮ)
ለተጨማሪ መረጃ
https://www.facebook.com/AACIDB
Telegram Adress
Website Address
https://www.industrydevelopment.gov.et
Youtube Adress
https://www.youtube.com/channel/UCfh4g0AVsFaHY2s0CnSRkj
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments