ዛሬ በነገዋ የሴቶች ተሀድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ...

image description
- In Uncategorized    0

ዛሬ በነገዋ የሴቶች ተሀድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ በአስከፊ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ የተሰጣቸውን ስልጠና በብቃት እና በተሳካ ሁኔታ ያጠነቀቁ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኝ ሴቶችን አስመርቀናል።

 

ተመራቂ ሰልጣኞቹ በአምስት ዲፓርትመንት፣ በአስራ ስምንት የሙያ ዘርፎች ላለፉት አራት ወራት ስልጠና በመውሰድና የስነ ልቦና ምክር በማግኘት ከነበሩበት አስከፊ የኑሮ ሁኔታ ለመውጣት ድጋፍ ሲደረግላቸው የቆዩ እንዲሁም በቀጣይ በስራ ሂደት ክትትል እና ድጋፍ የምናደርግላቸው ሲሆን፣ ሁሉም ሰልጣኞች የስራ እድል ተፈጥሮላቸው የመስሪያ ቦታ ቁልፎችን በዛሬው ዕለት ተረክበዋል።

ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት ከተማን ለመገንባት በጀመርነው ስራ ለወገኖቻችን የተስፋ ብርሀን በመፈንጠቅ ተስፋን የሚያለመልሙ ሰው ተኮር ስራዎችን እንድንሰራ ከጎናችን የቆማችሁ ልበ-ቀና ባለሃብቶችን በተመራቂ ተማርዎቹ ስም በድጋሚ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ብሩህ ተስፋ የሰነቃችሁ ውድ የነገዋ የተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ የመጀመሪያ ዙር ተመራቂ ሰልጣኞች እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ በተሰማራችሁበት የሙያ ዘርፍ ውጤታማ በመሆን ለሌሎችም ምሳሌ እንድትሆኑ አደራ እላለሁ።

ይህ ጅማሮ ነው፣ ገና በርካታ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስብራት የደረሰባቸውን ሴቶች ህይወት መጠገን ይጠበቅብናልና ትብብራችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለባለድርሻ አካላት ሁሉ ጥሪ ማድረግ እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments