የአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን ጠቅላ...

image description
- In Uncategorized    0

የአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር ) በተገኙበት አስጀምረናል፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር ) በተገኙበት ዛሬ አስጀምረናል ብለዋል ፡፡

በ35 ሄክታር መሬት ላይ ከቻይናው CCCC ጋር በአጋርነት የሚገነባው የአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በከተማ ውስጥ አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።

በውስጡ ትላልቅ ሞሎችን፣ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን፣ ቢሮዎችን፣ የትምህርት ተቋማትን፣ የጤና ተቋማትን እንዲሁም ሰፋፊ የመዝናኛና የውሃ አካላትን፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላትን ያካተተ ነው።

ይህ የአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለከተማችን አዲስ ገፅታ የሚያላብስ፣ ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚያጎላ፣ ተጨማሪ የውበት ምንጭ የሚሆን፣ ለነዋሪዎች ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር፣ ንግድን የሚያሳልጥ ነው።

ትልቅ ዓለም አቀፍ የግብይት ማዕከል የሚሆን እንዲሁም ማህበራዊ አገልግሎቶች የሚሰጡ መሰረተ ልማቶችን ያካተተ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናልም ብለዋል ከንቲባዋ በመልእክታቸው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments