
ቀጣይነት ያለዉ ኢኮኖሚ ለማምጣት ኢንዱስትሪዉን ብቃት ባለዉ አመራር እና ባለሙያ መምራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
አምራች ኢንዱስትሪዎች የዉጭ ምንዛሬ በማስገኘት፣በስራ እድል ፈጠራ እና ተኪ ምርት በማምረት ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ ሚና እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮም በከተማዋ ለሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች አስፈላጊዉን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ዘላቂ ምርታማነትን ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ ዘርፍ የእንጨት፣ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት በበጀት ዓመቱ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አቅም ለማጎልበት ከክፍለ ከተማ ቡድን መመሪዎች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር በ2017 በጀት ዓመቱ እቅድ ላይ ዉይይት አካሂዷል፡፡
ዉይይቱ በዋናነት ባለፈዉ ዓመት የነበሩ ክፍተቶችን በማስተካከል እና ከክፍለ ከተሞች ጋር በመናበብ በበጀት ዓመቱ የተሻለ ስራ ለመስራት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
በዘርፉ የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች አቅም ለማሳደግና ቀጣይነት ያለዉ ኢኮኖሚ ለማምጣት ብቁ አመረራርና እና ባለሙያ መፍጠር እንደሚገባ የእንጨት፣ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት አቶ ሀብታሙ እሸቴ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም በ2017 በጀት ዓመት ስራዎችን በወቅቱ በመገምገምና በቅንጅት በመስራት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አቅም ለማጎልበት በየደረጃዉ ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች በትኩረት መስራት እንደሚገባቸዉ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡
በሁሉም ክፍለ ከተሞች በዘርፉ የተሰማሩ 1,142 አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዳሉ ተገልጿል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments