
‘’በተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ስራዎች የታየው የመፈጸም አቅም በቀሪ ምዕራፍ ስራዎች ላይም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል” ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
በተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ስራዎች የታየው የመፈጸም አቅም በቀሪ ምዕራፍ ስራዎች ላይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ ተናገሩ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ ለኢዜአ እንደገለጹት በከተማዋ የተጠናቀቁትን ጨምሮ በመገንባት ላይ ያሉት የኮሪደር ልማት ስራዎች የአዲስ አበባን ገጽታ በመቀየር ተወዳዳሪነቷን ከፍ ያደረጉ ናቸው ብለዋል።
ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢኮኖሚ መነቃቃትን ለመፍጠር እንደሚያግዝም እንዲሁ፡፡
ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ በመፍጠርና የስራ ባህልን በመቀየር ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ነው የጠቆሙት፡፡
በመጀመሪያው ምእራፍ ተገንብተው የተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል ብለዋል።
በቀጣይም በአራት ኪሎ አካባቢ እየተገነባ ያለው ''አራት ኪሎ ፕላዛ'' የገበያና የመዝናኛ ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች የኮሪደር ልማት አካል የሆኑ ግንባታዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አብራርተዋል።
በመሆኑም በተጠናቀቁት የኮሪደር ልማት ስራዎች ላይ የታየውን የመፈጸም አቅም የማስቀጠል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የገለጹት፡፡
አመራሩ በኮሪደር ስራዎች ላይ ከህዝቡ ጋር ተቀራርቦ መስራቱን አስታውሰው፤ ህዝቡም የልማት ስራው ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም በከተማዋ ለሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ህዝቡ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments