
የአምራች ኢንዱስትሪውን የማምረት አቅም ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2016 እቅድ አፈፃጸምና በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ጀንጥራር አባይ እንደገለጹት በ2016 በጀት ዓመት ከባለድርሻ አካለት ጋር በቅንጅት በመስራት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የተሻለ ድጋፍ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡
የአምራች ኢንዱትሪዎች ምርትና ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር አስፋለጊ ነው ያሉት የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ስራ የአንድ ተቋም ስራ ባለመሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በ2017 ዓ.ም አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያነሷቸውን የመሰረት ልማት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የመሳሪያ ሊዝ፣ የጥሬ እቃ አቅርቦት፣ የውጭ ምንዛሬ እና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን ለመመለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እንደሚሰራ የተከበሩ አቶ ጃንጥራ አባይ ገልጸዋል፡፡
በ2017 ዓ.ም በጋራ ለመስራት የሚያስችል የጋራ የሥምምነት ሰነድ ከባለድርሻ አካለት ጋር የተፈራረሙ ሲሆን በ2016 ዓ.ም የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉ ተቋማት እውቅና ተሰጥቷል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments