
በደሴ ከተማ ለሚካሄደው የኮሪደር ልማት አስፈላጊውን የአመራር ድጋፍ እናደርጋለን፡፡
ከደሴ ከተማ አስተዳደር የመጡ የኮሪደር ሥራ አስተባባሪዎች በአዲስ አበባ ያለውን የኮሪደር ልማት ጉብኝት እና ግምገማ አደረጉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰሩ የኮሪደር ልማት ላይ ተሞክሮ ለመውሰድ የመጡት አስተባባሪዎች በደሴ ከተማ ለሚተገበረው የኮሪደር ልማት ተሞክሮ ለመውሰድ የሚረዳ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ለደሴ እና ሠመራ ከተማ የክሪደር ልማት የአመራር ድጋፍ እንዲያደርጉ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ( ዶ/ር) በተመደቡት መሠረት ከደሴ ከተማ አስተዳደር ከመጡ የኮሪደር ልማት ሥራ አስተባባሪዎች ጋር ዉይይት አካሂደዋል፡፡
በደሴ ከተማ ለሚካሄደው የኮሪደር ልማት የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ህብረተሰቡን አወያይተው መግባባት ከደረሱ በኋላ ስራውን መጀመር እንደሚገባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ገልጸዋል፡፡
አቶ ጃንጥራር አክለውም በደሴ ከተማ ለሚካሄደው የኮሪደር ልማት አመራሩ 24/7 መስራት እንደሚገባቸው አሳስበው አስፈላጊውን የአመራር ድጋፍ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተካሄው የኮሪደር ልማት ዉጤታማነት ከተማ አስተዳደሩ እና የከተማው ነዋሪ ህብረተሰብ ተቀናጅቶ እና ተመካክሮ በመስራቱ እንደሆነ አቶ ጃንጥራር ገልጸዋል፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሽመልስ ጌታቸው በበኩላቸው ከአዲስ አበባ ከተማ ኮሪደር ልማት ቁርጠኘነት እንደተማሩና የአላማና የተግባር አንድነትን እንዳዩ ገልጸዋል፡፡
የደሴ ከተማ ነዋሪም ቀናኢ አመለካከት ያለው ህብረተሰብ በመሆኑ በከተማችን የምንሰራው የኮሪደር ልማት ስኬታማ እንደሚሆን አቶ ሽመልሽ ገልጸዋል፡፡
አቶ ሽመልስ አክለውም ከአዲስ አበባ ከተማ አመራር ጥሩ ልምድ እንደወሰዱ እና በከተማ አስተዳደሩ የተካሄደው የኮሪደር ልማት ሰው ተኮር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነት እየተከናወኑ የሚገኙ የከተማዋ የኮሪደር ልማት በቀጣይ በተለያዩ የክልል ከተሞች የሚከናወን ይሆናል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በደሴ እና ሠመራ ከተማ አስተዳደሮች የሚከናወኑ የኮሪደር ልማቶችን ከአዲስ አበባው መስቀል አደባባይ መገናኛ ድረስ ካለው የኮሪደር ልማት ጋር በመደረብ በአስተባባሪነት ይመሩታል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments