ከአፋር የመጡ የኮሪደር ሥራ አስተባባሪዎች በአዲስ አበባ ያለውን የኮሪደር ልማት ጉብኝት እና ግምገማ አደረጉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ እስተዳደር የተሰሩ የኮሪደር ልማት ላይ ተሞክሮ ለመውሰድ የመጡት አስተባባሪዎች በሠመራ ከተማ ለሚተገበረው የኮሪደር ልማት ተሞክሮ ለመውሰድ የሚረዳ ነው።
አቶ ጃንጥራር አባይ ለሠመራ ከተማ እና ደሴ ከተማ የክሪደር ልማት የአመራር ድጋፍ እንዲያደርጉ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ዶ/ር) በተመደቡት መሠረት ቀደም ብለው ሁለቱንም ከንቲባዎች በአዲስ አበባ የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በመጡበት ወቅት ስለያዙት እቅድ ከእያንዳንዳቸው ጋር ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው::
በዚህም ስራውን በሁለቱ ከተሞች ለማስጀመር የአዲስ አበባን ኮሪደር ልማት ማስጎብኘት እንደሚገባ በተደረሰው ስምምነት በዛሬው እለት ማለትም መስከረም 6/2017 ዓም የሰመራ ከተማ ልኡክ ጉብኝት በማድረግ ከክቡር ምክትል ከንቲባው ጋር ድጋፍ የሚያደርጉ አመራሮችና ባሐሙያወች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱም ለቀጣይ ሥራ ጠቃሚ አሥተያየቶች ተሰጥተዋል።
በዚህ የጉብኝት እና ግምገማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአምራች ኢንዱስትሪ ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ኩሳ፣ ከፕላን ልማተ ቢሮ አቶ ኡመር ደሴ፣ ከአረንጓዴ ልማት ቢሮ አቶ ነጋሽ አረጋ፣ ከሠመራ-ሎግያ ከተማ አስተዳደር የከተማ አገልግሎት ሥራ አሰኪያጅ፣ ከአፋር ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ የተወከሉ ባለሙያዎች እና አማካሪዎች የልዑክ ቡድን በጉብኝቱ ተሳትፈዋል።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነት እየተከናወኑ የሚገኙ የከተማዋ የኮሪደር ልማት በቀጣይ በተለያዩ የክልል ከተሞች የሚከናወን ይሆናል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምከትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በደሴ እና ሠመራ ከተማ አስተዳደሮች የሚከናወኑ የኮሪደር ልማቶችን ከአዲስ አበባው መስቀል አደባባይ መገናኛ ድረስ ካለው የኮሪደር ልማት ጋር በመደረብ በአስተባባሪነት ይመሩታል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments