












አምራች ኢንዱስትሪውን በጥራትና በብቃት ለመደገፍና የማምረት አቅምን ከፋ ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ለባለሙያዎች እየተሰጠ ነው።
አምራች ኢንዱስትሪውን በጥራትና በብቃት ለመደገፍና የማምረት አቅምን ከፋ ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ለባለሙያዎች እየተሰጠ ነው።
የአምራች ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ ዘርፍ የአግሮ ፕሮሰሲንግ እና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት በሁሉም ክ/ከተማ ለሚገኙ ለዘርፉ ቡድን መሪዎች፣አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነው።
ስልጠናው የባለሙያዎችን አቅም በማጎልበትና የመደገፍ ክህሎታቸውን በመጨመር፤ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት የማምረት አቅምን ለማሻሻልና ጥራት ያለው ምርት ለማምረት እንደሚረዳቸው የአግሮ ፕሮሰሲንግ እና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ታሪኳ ተሰማ ገልጸዋል፡፡
ዳይሬክተሯ አያይዘውም ስልጠናው በአግሮ ፕሮሰሲንግና ፋርማስሲዩቲካል ዙሪያ፡ምግብን በማዕድን ማበልፀግ፣ተኪ-ምርት ማምረት፣ የምረት ቴክኖሎጂን መጠቀም እና ደረቅ ቆሻሻና ፍሳሽ አወጋገድ ላይ ትኩረት ያደረገ ሰልጠና ሲሆን ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
መስከረም 22፣2017 ዓ.ም (አ.ል.ቢሮ)
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments