ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የሚመጥን ድጋፍ ለማድረግ የባለሙያውን አቅም በስልጠና ማሳደግ እንደሚያስፈለግ ተገለጸ፤
የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የአምራች ኢንዱስትሪ ድጋፍ ዘርፍ ለክ/ከተማ የዘርፉ ቡድን መሪና ባለሙያዎች የመጀመሪያ ዙር የስራ ላይ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ላይ ንግግር ያደረጉት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአምራች ኢንዱስትሪ ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ኩሳ እንደገለጹት ቢሮው የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ባለሙያዎች ሙያዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ክህሎታቸውን የሚያሳድግ ስልጠና አስፋለጊ ነው ብለዋል፡፡
ኃላፊው አያይዘው የባለሙያዎችን ክህሎት የሚያሳድጉ ተከታታይ የተግባር ላይ ስልጠናዎች እንደሚሰጥ ጠቁመው በተጨባጭ በተግባር ላይ በሰለጠኑት ስልጠና መሰረት የአምራች ኢንዱትሪዎች ምርትና ምርታማነት ከፍ የሚያደግርግ ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
የቆዳና ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉሃብት ገነት በበኩላቸው ስልጠናው በቆዳና ጨርቃጨርቅ ላይ የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ቴክኒካል የሆነ ድጋፍና የማማከር ስራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ገልጸው የሚመለከታቸው የዘርፉ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ናቸው ብለዋል፡፡
ስልጠናው ተግባር ላይ ያተኮረ በመሆኑ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ሙያዊ የሆነ ድጋፍ ለማድረግ በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ሰልጣኞች ገልጸዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments