







የአምራች ኢንዱስትሪዎች የመሬት እና የመስሪታ ቦታ ጥያቄ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲያገኝ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪዎች የመሬት እና የመስሪታ ቦታ ጥያቄ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲያገኝ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አአስተዳደር የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ገለፀ።
ቢሮው የ2017 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ከ11ዱም ክፍለ ከተማ የጽህፈት ቤት አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የመሬት እና የመስሪታ ቦታ ጥያቄ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲያገኝ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ጃንጥራር ለዘርፉ አመራሮች ኢንዱስትሪን በብቃት መምራት የሚያስችል አቅም እንዲኖራቸው የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በውይይቱ በሩብ ዓመት አፈጻጸም ላይ በጥንካሬ የተነሱ በርካታ ስራዎች የተከናወኑ ቢሆንም ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ ባለው የአስተዳደር እርከን ተናባቢ ያልሆነ እና የተጣረሰ ሪፖርትን በማስቀረት እና ለተግባር ምዕራፍ ስኬታማ ስራ ለመስራት እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
የውይይት መድረኩ ተሳታፊ አመራሮችም የአምራች ኢንዱስሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments