ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 20ኛውን የኢትዮጵያ ብ...

image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል አስተናጋጅ ክልል ሆነ

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በአል አስተናጋጅ ክልል መሆኑ ተገለፀ ፡፡

የቀጣዩን 20ኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በአል አስተናጋጁ ማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮጵያ ሰንደቅአላማ ተረክቧል ፡፡

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫም ባለፈው አንድ አመት በሶማሌ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሲዘዋወር መቆየቱ ይታወቃል ፡፡

ያለፈው አመት የህዳሴ ግድብ ዋንጫ የሶማሌ ክልል ተረክቦ የነበረ ሲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህና የሶማሊያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ኡመር ዋንጫውን ለተረኛው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ አስረክበዋል ፡፡

19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች "ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአርባምንጭ ከተማ እየተከበረ ይገኛል ፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments