




ለኢንተርፕርይዞች እና ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ መረጃቸውን ማጥራት እና በማደራጀት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለኢንተርፕርይዞች እና ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ከስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመረጃ አያያዝ ላይ ከክፍለ ከተማ የዘርፉ ቡድን መሪዎች ጋር ዉይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ የተገኙት በኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የፋሲሊቴሽንና ካይዘን ትግበራ ዘርፍ ኃላፊ ኤፍሬም ግዛው (ዶ/ር) ሁለቱም ቢሮዎች በዋናነት አምራች ኢንዱስትሪዎችን የመደገፍ እና የማበረታታት ስራ አንደሚሰሩ ገልጸው ስራዎችን በቅንጅት መምራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ኃላፊዉ አክለዉም ከሁለቱም ተቋማት በተቀናጁት ኮሚቴዎች አማካኝነት በሁሉም ክፍለ ከተማ የሚገኙ ኢንተርፕርይዞች እና አምራች ኢንዱስትሪዎችን መረጃ በጥራት መሰብሰብ እና ማደራጀት እንዳለባቸው አሳስበው አመራሮችም በትኩረት ክትትል እንደሚያደርጉበት ገልጸዋል፡፡
በስራና ክህሎት ቢሮ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የኢንተርፕራይዞች ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ ሌጋኒ በበኩላቸው ለኢንተርፕርይዞች እና ለአምራች ኢንዱስትሪዎች አስፈላጊዉን የእድሳት እና የደረጃ እድገት ለመስጠት ተገቢዉን መረጃ በቅንጅት ማደራጀት እንደሚገባ ገልጸው በአሰራር ላይ የሚገጥሙ ችግሮችን መመሪያዎችን መሰረት በማድረግ እንደሚፈታ አሳስበዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments