





አምራች ኢንዱስትሪዎችን መደገፍ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት አወንታዊ አበርክቶ እንዳለው ተገለጸ።
በከተማ አቀፍ የሚዘጋጀው የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ዐውደ ርዕይና ባዛር በኮልፌ ቀራኒዮ እና በየካ ክፍለ ከተሞች በይፋ ተጀምሯል።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ሶስት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን አምራቹንና መንግስትን በማገናኘት የበርካታ አምራች ኢንዱስትሪዎች ጥያቄ ለመመለስ እድል ከፍቷል ብለዋል።
የአምራች ኢንዱስትሪዎች አበርክቶ እና እድገት ገና ያልተነካ ዘርፍ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው በየደረጃው ያለው አመራር አምራቹን በመደገፍና ጥያቄያቸውን መመለስ የማምረት አቅም በሀገር አቀፍ ደረጃ ወደ 11 .9 በመቶ ከፍ ለማድረግ ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት አየሰራ ነው ብለዋል።
አምራች ኢንዱስትሪዎች ማህበራዊ ሀላፊነትን በመወጣትና ገበያውን በማረጋጋት ሚናቸው ከፍ ያለ በመሆኑ ምርታማነታቸውን በማሳደግ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አሳስበዋል ።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ የኔው ሞሴ በበኩላቸው የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሻሻል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በልዩ ትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
በተጨማሪም በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በቴዎድሮስ ፍቅሩ ኢንዱስትሪ በጎ ፍቃደኝነት የሚካሄደውን የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት ፕሮግራምን የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ አስጀምረዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments