









በበለይነህ ክንዴ ፋውንዴሽን በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ወገኖች በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የተገነባው የጋራ መኖሪያ ህንጻ ለነዋሪዎች ተላለፈ።
በምረቃ ስነ-ስርአቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ መንግስት እና የግል ባለሀብቱ እንዲሁም ህዝቡ በጋራ ከተቀናጀና ከተባበረ የማይመጣ ለውጥ የለም ብለዋል።
አገር የሚቀየረው በአንድ ጊዜ ሳይሆን ባለው ላይ እየጨመሩ በመስራት ነው ያሉት አቶ ጃንጥራር አቶ በላይነህ ክንዴ ላደረጉት በጎ ተግባር በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
አቶ ጃንጥራር አክለውም የቤቱ ተጠቃሚ የሆናችሁ ዜጎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልካም የገና በአል ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የበላይነህ ክንዴ ፋውንዴሽን ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ በበኩላቸው መንግስት የህብረተሰቡን ኑሮ ለመቀየር በሚያደርገው እንቅስቃሴ ድርጅታቸው ከወገናቸው ጎን በመሆን የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሆነ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ለግንባታው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments