የኢንዱስትሪዎችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ከመንግስት እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ
የአዲስ አበባ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት 17ኛው መደበኛ ጠቅላላቅ ጉባኤ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ምክት ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በአምራች ኢንዱስትሪው የሚታየውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት ከባለ ድርሻ ተቋማት ጋር በትብብር እየተወያየ ችግሮችን ሲፈታ የቆየ ሲሆን አምራች ኢንዱስትሪውም ማህበራዊ ተሳትፎውን በአግባቡ ሲወጣ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡
የዘርፍ ማህበራት ለአምራች ዘርፉ የተለያዩ አገልግሎቶችን በራሳቸው ተቋማት እንዲያገኙ፣ የአባላቶቻቸው መብት እና ጥቅም እንዲከበር፣ የሀገሪቱ ምርቶች እንዲተዋወቁ እና ተኪ ምርቶች እንዲበረታቱ፤ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ እና በመንግስት እና በአምራቹ ዘርፍ መካከል እንደ አገናኝ ድልድይ ሆነው እንዲሰሩ በማድረግ ራሳቸውን ችለው በማይክሮ እና በማክሮ ኢኮኖሚ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያጎለብቱ እና አለማቀፋዊ ተሳትፎቸውን ማሳደግ እንደሚገባቸው አቶ ጃንጥራር ገልጸዋል።
ባለፉት ሦስት ዓመታት የተጀመረው የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ፕሮግራም ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ያሉ አዲስ የኢንዱስትሪ ፖሊሲን በማሻሻልና ስትርቴጂዎችን በመንደፍ ለአምራቹ ዘርፍ ድጋፍ በማድረግ በአመራሩ ቁርጠኝነት እየተተገበሩ መሆኑን ክቡር አቶ ጃንጥራር ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የቀጣይ የማህበሩ መሪ በፍትሐዊ መንገድ ለማህበሩና ለአምራች ኢንዱስትሪዎች በሚጠቅም መልኩ እንዲመርጡ አቶ ጃንጥራር አሳስበዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments