የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ማስጀመሪ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ማስጀመሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተካሄደ።

የ2017 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ  ፕሮግራም የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች የክፍለ ከተማ አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት  ተካሂዷል።

በመድረኩ  የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በቢሮ  ኃላፊ  ደረጃ  የፋሲሊቴሽንና ካይዘን ትግበራ ዘርፍ  ኃላፊ  ኤፍሬም  ግዛው ( ዶ/ር)  የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ከሚደግፋቸው  ሴክተሮች  አንዱ የኢንዱስትሪ ልማት  መሆኑን ገልጸው  ውጤታማና ጥራት ያለው የማምረት አቅም ለማሳደግ የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ መድረክ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች መልካም ዕድል የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

የማኑፋክቸሪንግ ዘርፋ ላይ ትኩረት በማድረግ ድጋፍና ክትትል ለሚሹ አምራች ኢንዱስትሪዎች  ማነቆዎችን በመፍታት ለኢኮኖሚ  ያላቸውን  ሚና እንዲያበረክቱ  ለማድረግ ንቅናቄው ወሳኝ እንደሆነ ዶክተር  ኤፍሬም ገልጸዋል።

ዶክተር ኤፍሬም አክለውም የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ በዚህ ዓመት በልዩ ትኩረት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ማነቆች ለመፍታት ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአምራች ኢንዱስትሪ ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ኩሳ በበኩላቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች ለሀገር የኢኮኖሚ እድገት የራሳቸውን ሚና መጫወት እንዳለባቸው ገልጸው ዜጎች ማህበረሰቡ የሀገራቸውን ምርት መጠቀምና ማበረታታት እንደሚጠበቅባቸውና በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አመለካከታቸውን የቀየረና በሀገር ምርት የመኩራት እሳቤ ያጎናጸፈ ነው ብለዋል።

የሌሎች ሀገር ዜጎችም የሀገራችንን ምርት እንዲጠቀሙ ማበረታታት እና ለአፍሪካ ህብረት ለሚመጡ እንግዶች ምርትና አገልግሎትን በመሸጥና በማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ በመሆኑ አምራች ኢንዱስትሪዎች ይህንን መልካም አጋጣሚ እንዲጠቀሙ አቶ ጳውሎስ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ከፍተኛ አመራሩ በክፍለ ከተማ የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት የተዘጋጀውን አውደርዕይ እና የአምራች ኢንዱስትሪዎች ምርት እና አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ማሽኖችን ጎብኝተዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments