ግብረ ሀይሉ ህገወጥነትን ለመከላከል፣ ገበያውን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

ግብረ ሀይሉ ህገወጥነትን ለመከላከል፣ ገበያውን ለማረጋጋትና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የገበያ ማረጋጋት፣ ገቢ መሰብሰብ፣ ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር የኢትዮጵያ  አዲስ አበባ ታምርት ግብረ ሀይል  የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ላይ ውይይት አድርጓል።

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ  እና የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ   ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት ግብረ ሀይሉ ከተቋቋመ  ወዲህ የምርት አቅርቦትና ምርታማነትን በማሳደግ፣ ህግ በማስከበር እንዲሁም ለህብረተሰቡ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ በቅንጅት በተሰራው ስራ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል  ብለዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት የምርት እጥረትና  የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር፣ የኩፖን ስርጭት በመጀመር፣ በኮሪደር ልማት የተነሱ የሸማች ሱቆችን  ምትክ በመስጠት፣ ህገወጥነትን በመቆጣጠርና በመከላከል፣  የሚዲያ ሽፋን በመስጠት፣  የገቢ አሰባሰብ ስራን በማጠናከር፣ የቅዳሜና እሁድ ገበያ በማስፋት እንዲሁም  ግብረ ሀይሉ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራቱ የተሻለ አፈጻጸም  መመዝገቡን በቀረበው ሪፖርት ላይ ተመላክቷል።

የግብረ ሀይሉ ተሳታፊዎች  በበኩላቸው የተሰሩ ስራዎች በህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ላይ እሴት የሚጨምሩ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ወራቶች የተሻለ ስራ ለመስራት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የመሰረተ ልማትና ተያያዥ  ጥያቄዎችን በመመለስ፣ በኮሪደር ልማት ለፈረሰባቸው ሸማች ማህበራት ምትክ ቦታ በመስጠት እና ምርት ለመከዘን የሚያስችል ቦታ ማዘጋጀት  በአንድ ተቋም የሚፈጸም ባለመሆኑ ትኩረት በመስጠት በቅንጅት ተናበው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

በመጨረሻም የእቅድ ክለሳን በማድረግ፣ የምርት አቅርቦትንና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የሸማች ማህበራት በማጠናከር፣  የቁጥጥርና ህግን የማስከበር ስራ ማጠናከር፣ የገቢ አሰባሰብ ችግርን መፍታት እንዱሁም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ችግር መፍታት በቀጣይ  ትኩረት የሚሰጣቸው ተግባራት በመሆናቸው ግብረ ሀይሉ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ አሳስበዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments