''የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

''የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ፡፡

ቢሮው  ከባለድርሻ  አካላት ጋር በተሰሩ ቅንጅታዊ አሰራሮች እና በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ  የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት  ላይ የባለድርሻ አካል ተቋማትና የክፍለ ከተማ የጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም  የዘርፍ ማህበራት ሰብሳቢዎች በተገኙበት ውይይት  አካሂዷል።

ባለፉት ስድስት ወራት ቢሮው ከባለድርሻ  ተቋማት ጋር  በቅንጅት በመስራት የአምራች ኢንዱስትሪዎች  የመሠረተ ልማት ችግሮች የተፈታበት እና ተጨባጭ ውጤት የታየበት እንደነበር የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ገልጸዋል።

ጥራት  ያለውና ተወዳዳሪ ምርት በማምረት  የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ  የአምራች ኢንዱስትሪዎች ሚና ከፍተኛ  በመሆኑ ባለድርሻ አካላት  ኢንዱስትሪዎችን ለማጠናከር ችግሮችን በመለየት   ተገቢውን  ድጋፍ ማድረግ   እንዳለባቸው ምክትል ከንቲባ  አቶ ጃንጥራር ገልጸዋል።

ምክትል ከንቲባው አክለውም አምራች ኢንዱስትሪዎች ለሀገራችን ኢኮኖሚ ባላቸው ድርሻ  መሠረት  በፋይናንስና ብድር፣ በግብዓት አቅርቦት፣ በመሳሪያ ሊዝ በመደገፍ የማምረት አቅማቸውን ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም  በቀጣይ ስድስት ወራት  ባለድርሻ አካላት አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደ ሀገርም እንደ ከተማም ያላቸውን ፋይዳ በመረዳት  የተጠናከረ ደጋፍ ማድረግ  እንደሚገባ ምክትል  ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አሳስበዋል።

ቢሮው  በበጀት አመቱ መጀመሪያ ከባለድርሻ  አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት የስምምነት ሰነድ መፈራረሙ ይታወሳል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments