








''የኅብረት ሥራ ማህበራትን ማጠናከር ለሸማች ህብረተሰቡ ያለው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለጸ''
''የኅብረት ሥራ ማህበራት ሚና ለኢትዮጵያ ብልጽግና'' በሚል መሪ ቃል በኢግዚቢሽን ማዕከል የኅብረት ሥራ ኤግዚቪሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚየም በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ የኅበረት ሥራ ማህበራትን በማጠናከር ለሸማች ህብረተሰቡ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ማህበራትን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ኅብረት ሥራ ማህበራት ለሀገር ዕድገት ባለቸው ሚና መሠረት እንዲጠናከሩ ከመስራት አንፃር በትብብር መንፈስ አደረጃጀትንና አሠራርን ማጠናከር እንደሚገባ አቶ ጃንጥራር ገልጸዋል።
በቀጣይ ከክልሎች ጋር ያለው የተቀናጀ ሥራ ግንኙነት እንዲልቅ በማድረግና የክልል አመራሮች በአካባቢያቸው ያሉ ምርቶችን ወደ ግብይት እንዲገቡ የማድረግ ሚናቸውን እንዲወጡ አቶ ጃንጥራር አሳስበዋል።
በመጨረሻም የተወካዮች ምክርቤት አባላት፣ ሚኒስትሮች፣ አባሳደሮች እና የከተማው ከፍተኛ አመራሮች የኅብረት ሥራ ማህበራት ምርት እና አገልግሎቶችን ጎብኝተዋል።
ይህ የኅብረት ሥራ ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚየሙ እስከ የካቲት 3 ለሸማቾች ክፍት ይሆናል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments