የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ተኛ አመ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ተኛ አመት 7ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

1 በከተማዉ  አስተዳደር በጀት ተመድቦላቸዉ የተገነቡ እና በመጠናቀቅ ያሉትን  አዳዲስ ሆስፒታሎችን ዘመኑን በዋጀ ህክምና መሳሪያ ለማሟላት እና አለም አቀፍ ደረጃን የሚያሟላ  አገልግሎት መስጠት ያስችላቸው ዘንድ    በዘርፉ ትልቅ ልምድ ካከበቱ የግል ሴክተር ጋር በአጋርነት ለመስራት ዉሳኔ አሳልፏል።

 

2ኛ አንዳንድ የመንግስት አገልግሎቶችን በውል ለ3ተኛ ወገን ለማስራት የወጣውን ረቂቅ  ደንብ መርምሮ በማየት ካቢኔዉ አፅድቋል።

 

3ኛ  የተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ላላቸው እና ተኪ ምርቶችን ለሚያመርቱ ኢንዲስትሪዎች ባቀረቡት የማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎች ላይ ለጥልቅ በመወያየት እና የአተገባበር አቅጣጫ በማስቀመጥ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

 

4ተኛ የኮሪደር ልማት ውጤት ከሆኑት ሥራዎች አንዱ የብዙሀን ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ችግሮች የሚያቃልል እና የትራፊክ ፍስቱን የሚያሻሽለው የብስክሌት መጋራት አገልግሎት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብን በመመርመር አፅድቋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments