







የ6 ወራት የስራ ዕቅድ አፈጻጸማችንን ግምገማ አጠናቅቀናል፡፡
በግምገማችን ባለፉት ስድስት ወራት መገንባት የጀመርነዉን ጠንካራ የስራ ባህል የአመራር ቁርጠኝነትንና ቅንጅትን በማጠናከር እንዲሁም የገቢ አሰባሰብን በማሳደግ በርካታ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜና በጀት በጥራት አጠናቅቀን ለህዝባችን ግልጋሎት ክፍት አድርገናል::
የሀገርን ክብርን በሚመጥን መልኩ ውብ፣ ጽዱ እና ለመኖር ምቹ ለማድረግ የጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራ አዲስ አበባን አለም አቀፍ የስበት ማዕከል ከማድረግ በተጨማሪ ለነዋሪዎቻችን ምቹ የመኖሪያ አካባቢ እና ሰፊ የስራ እድል የፈጠሩ፣ አገልግሎትን የሚያሳልጡ ተግባሮች ተከናዉነዋል፣ የተቀሩትንም በቀሪ ወራት በፍጥነት የምናጠናቅቅ ይሆናል።
በቀጣይም የአፈፃፀም ዉስንነትን በማስተካከል፣ ማዘመን የጀመርነዉን አገልግሎት አሰጣጥን በማጠናከር ቀልጣፋ እና ፈጣን እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ተደራሽ በማድረግ፣ ብልሹ አሰራር እና ጉቦኝነትን በመታገል እንዲሁም የገቢ አሰባሰብ እና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የተጀመሩ ስራዎችን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት የምንሰራ ይሆናል::
ከከተማችን ነዋሪዎች ጋር በመተባበር ድክመቶቻችንን ከነመንስዔዎቻቸው ተነቅሰው እንዲታረሙ እያደረግን ለላቅ ውጤታማነት መትጋታችንን የምንቀጥል ይሆናል::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments