የተቀናጀ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የድጋፍና ክትት...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

የተቀናጀ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የድጋፍና ክትትል ሥራ ለምርት ጥራትና ውጤታማነት ወሳኝ ነው።

የማዕከል የዘርፉ ዳይሬክተሮች፣ የክፍለ ከተማው የኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ እና የሥራ አስተባባሪዎች በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ የተቀናጀ የድጋፍና ክትትል ሥራየመስክ ምልከታ ድጋፍና ክትትል አደረጉ።

 

የእንጨት ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ እሸቴ ድጋፍና ክትትሉ  የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ሙያዊና ቴክኒካዊ ድጋፍና ክትትል ቀጣይነት ባለው መልኩ መስጠት ዓላማ ያደረግ እና ዘርፉን ለማጠናከር ዓላማ ያለው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

 

አምራች ኢንዱስትሪዎች በራስ አቅም የማምረቻ መሳሪያ ወይም ማሽነሪ በማምረት ቴክኖሎጅን ከመጠቀም አንፃር ለሀገርም ለአምራች ኢንዱስትሪዎች አቅም የሚፈጥሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን በመስክ ምልከታው ማረጋገጥ መቻሉን አቶ ሀብታሙ ገልጸዋል፡፡

 

የአግሮ ፕሮሰሲንግ እና ፋርማስቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ታሪኳ ተሰማ በበኩላቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች ንፁህ የአመራረት ዘዴን የተገበሩ አምራች ኢዱስትሪዎች ላይ መሆኑን ገልጸው የደረጃና የምርት ጥራት ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የምርት ስታንዳርድ ያዘጋጁና የተገበሩ፣ የምርት ጥራት ቁጥጥር ሥርዓቶችን የተገበሩ፣ ተረፈ ምርቶችን መልሶ መጠቀም የቻሉ እና የንፁህ የአመራረት ዘዴዎችን የተገበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎችን መደገፍ መቻል አምራች ኢንዱስትሪዎች መነቃቃት እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments