አብሮነት ለአገልግሎት አሰጣጥ እና ለአገልጋይ እ...

image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

አብሮነት ለአገልግሎት አሰጣጥ እና ለአገልጋይ እርካታ ከፍ ያለ ሚና እንዳለው ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሠራተኞችና አመራሮች በጋራ ወርቃማው ሰኞ የአብሮነት ቀንን በዛሬው ዕለት አከናወኑ፡፡

 

"አብሮነት ለአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል" በሚል መሪ ቃል የአብሮነትና አገልግሎት አሰጣጥ ፅንስ ሃሳብ እና የሠራተኛ ተሞክሮ ማቅረብ ተችሏል፡፡

 

በመድረኩ የተገኙት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአምራች ኢንዱስትሪ ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጰውሎስ ኩሳ ሰኞ እንደ ከተማ አሰተዳደር የአብሮነት ቀን በማለት በሠራተኞች ላይ መነቃቃትን የፈጠረ መሆኑን ገልጸው ይህ የአብሮነት ቀን ሠራተኛውን ከማነቃቃቱ በተጨማሪ የአገልጋይን እርካታ ከፍ በማድረግ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ለሪፎርም ሥራዎች ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡

 

በዕለቱ ተሞክሯቸውን ያካፈሉት የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት እና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል፤ ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ትልቅሰው በተለያዩ የመንግስት ተቋማት የተለያዩ ሥራዎች በማከናወንና በበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ መሳተፋቸውን ተሞክሮ አካፍለዋል፡፡

 

ይህ የአብሮነት ቀን በዕለተ ሰኞ ሁልጊዜም የሚቀጥል ሲሆን የሰራተኞችን አብሮነት እና የህይወት ተሞክሮ የሚያጠናክር ነው፡፡

 


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments