



የፋሲሊቴሽንና ካይዘን ትግበራ ዘርፍ ከክፍለ ከተማ የዘርፉ የሥራ አስተባባሪዎችና ከቡድን መሪዎች ጋር ባለፉት አስር ወራት የተሰሩ ሥራዎች በተሰጡ ግብረ መልሶችን በጋራ ገመገሙ፡፡
ባለፉት 10 ወራት በዘርፉ በርካታ ሥራዎች መከናወን መቻላቸውን በቀረበው ሰነድ ላይ ተመላክቷል፡፡
በገቢያ ትስስር፣ በኢግዚቢሽንና ባዛር፣ በግብዓት ትስስር፣ በኤክስፖርት እና በተኪ ምርቶች ላይ የተሻለ ሥራ በመሰራቱ በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ መነቃቃት መፍጠሩን በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
የካይዘን ፍልስፍና እና የማማከር ሥራዎች፣ የአቅም ግንባታ ሥራዎች፣ የምርታማነት ልኬት እና ከካይዘን ትግበራ በኋላ የዳነ ሃብት በበጀት ዓመቱ 10 ወራት የተከናወኑና ውጤታማ ሥራ የተከናወነባችው ተግባራት መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታና የመሠረተ በልማት ችግሮች ለመፍታት የተሄደበት መንገድ ባለፉት 10 ወራት ውጤታማ እንደነበር በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡
በሌላ በኩል በደረጃ ዕድገት ሽግግር ከጥቃቅን ወደ አነስተኛ እንዲሁም ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ የተሸጋገሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ዘመናዊ ሂሳብ መስመር ዝርጋታ እነዲሁም ሞዴል የአምራች ኢንዱስትሪ የተቀመረ ምርጥ ተሞክሮ በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ስኬታማ ውጤት ማሳየቱ ተካቷል፡፡
በመጨረሻም በቀጣይ ቀሪ ሁለት ወራት የሚከናወኑ ሥራዎችን በትኩረት እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments