"የኢንዱስትሪ እና የንግዱ ዘርፉ ሀገር ከምትመራ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

"የኢንዱስትሪ እና የንግዱ ዘርፉ ሀገር ከምትመራበት የኢኮኖሚ አቅጣጫ አኳያ ሚናው የላቀ ነው " ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ

ለሁለንተናዊ ብልፅግና ፣ የንግዱ ማህበረሰብ ሚና በሚል መሪ ቃል ከኢንዱስትሪ እና የንግድ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ተካሂዷል።

 

በውይይቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ባለፉት የለውጥ አመታት በፓለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በዲፕሎማሲ በርካታ ስኬቶች ማምጣት እንደተቻለ ገልጸው ዘርፉ ሀገር ከምትመራበት የኢኮኖሚ አቅጣጫ አኳያ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

 

ምክትል ከንቲባው አክለውም በግብርና ፣ በኢንዱስትሪ ፣ በቱሪዝም ፣ በማዕድን እና በዲጅታል ኢኮኖሚ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ከተቻለ እንደ ሀገር ለሚኖረን የሀገረ መንግሰት ግንባታ አስተማማኝነትና ዘላቂነት ማረጋገጥ እንደሚቻል ገልጸዋል።

 

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበር( ዶ/ር) በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ ከኢንዱስትሪ እና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት በመስራቱ በከተማ አስተዳደራችን በርካታ የልማት ስራዎች መስራት እንደተቻለ ገልጸው በቀጣይ ይህንን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments