ቢሮው በውስጥ ቁጥጥር ስርዓት ላይ የግንዛቤ ማስ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In Uncategorized    0

ቢሮው በውስጥ ቁጥጥር ስርዓት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በአሰራር ማእቀፎች፣ በፋይናስ ተጠያቂነት፣በስነ ምግባር ጥሰትና በሚያስከትሉ ጉዳዮች፣ በውስጥ ቁጥጥር ስርዓት እንዲሁም በሰው ሀብት አስተዳደር ዙሪያ ለሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

 

ስልጠናውን ያስጀመሩት የስነ ምግባርና ጸረሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ፍቅሬ እንደገለፁት ግለጽ የሆነ የአሰራር ተጠያቂነት ለመፍጠር የተቋሙን የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት አሰራር ለሰራተኞች ማሳወቅ ቀዳሚ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

 

የውስጥ ቁጥጥር ስርዓትን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበበ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

 

የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት የተቋምን ተልዕኮ ለማከናወን በማኔጅመንትና በሰራተኛው የሚከናወን ስጋትን የሚከላከል ሚዛናዊ ማረጋገጫ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

 

ወ/ሮ መዓዛ አክለውም በፋይናንስ ቁጥጥር፣ በበጀት ቁጥጥር፣ በሂሳብ ምዝገባና በስራ አመራር ቁጥጥር ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

 

የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለባቸው ሀይሌ በበኩላቸው በአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010 በተመለከተ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

 

ስልጠናውን ያዘጋጁት የስነ ምግባርና ጸረሙስና ዳይሬክቶሬት፣ የውስጥ ኦዲትና የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ናቸው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments